Warning: mkdir(): No space left on device in /var/www/tg-me/post.php on line 37

Warning: file_put_contents(aCache/aDaily/post/orthodox1/--): Failed to open stream: No such file or directory in /var/www/tg-me/post.php on line 50
ኦርቶዶክስ ተዋህዶ - ‌🇴‌🇷‌🇹‌🇭‌🇴‌🇩‌🇴‌🇽 ‌🇹‌🇪‌🇼‌🇦‌🇭‌🇩‌🇴 | Telegram Webview: orthodox1/13011 -
Telegram Group & Telegram Channel
ለ) ሁለተኛው ከላይ በመነሻነት የተቀመጡ የሦስቱን ወንጌላውያን መልእክት ስናነብ  በመጽሐፍ ቤት የሐዲሳቱ ሊቃውንት ደብረ ታቦር አልፎ በተናገረበት አውድ ሲፈቱ ትርጓሜውን ለዮሐንስ ሰጥተው «የእግዚአብሔር መንግሥት በኃይል ስትመጣ እስኪያዩ ድረስ፥ ሞትን የማይቀምሱ አንዳንዶች»  የተባለው እርሱን የሚወክል እንደሆነ ነግረዋል
አንዳንዶች ብሎ ማብዛቱ መጽሐፍ ስም ካልጠራ ማብዛት ልማዱ ነውና
ለምሳሌ ፦ በተአምኖ አመ ነገርዎ ለኖኅ (የነገረው አንድ መልአክ ሆኖ ሳለ) ፣ ብፅዕት አንቲ እንተ ተአምኒ ዘነገሩኪ (ያበሠረው አንዱ ቅዱስ ገብርኤል ሆኖ ሳለ)

በሌላ መልኩ ደግሞ በተቀሩት ሦስቱ ወንጌላውያን ተጠቅሶ በእርሱ አለመጻፉ ራሱን የሚመለከት ቢሆን ነው። ክብሬ ይገለጥልኝ መወደዴ ይነገርልኝ ብሎ ጉዳዩ እርሱው ራሱ ባለበት ተነግሮ ግን በወንጌሉ ሳያኖርልን የቀረው ስለትህትና  እንደሚሆን ይታመናል።

ሐ) ደብረታቦርን ካነሳን እግረ መንገድ ቅዱሱ አባታችን ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ በመጽሐፈ ምሥጢር  ምሥጢረ ታቦርን ደጋግሞ ከአማናዊት የሐዲስ ኪዳን መርጡል ጋር እያዛመደ አስተምሮበታል።  በሥፍራው የተገኘውን አልያስን አንስቶ ወደብሔረ ሕያዋን እንዴት እንደተነጠቀ ሲነግረን  «ወከበቶሙ እግዚአብሔር ውስተ ምድር ኅብእት እንተ ተሠወረት በጥበበ ዚኣሁ ወአልቦ ሥልጣነ ሞት» ይላል።
ታዲያ መሰሉን አብነት ይዘው መምህራን በቦታው የተገኘውን ኤልያስ ከዮሐንስ እንድናነጻጽር በማመላከት፤ አምላካችን ክርስቶስ እና ቅዱስ ጴጥሮስ በመስቀል ተሰቅለው ቢያልፉ ፣ ሊቀ ነቢያት ሙሴና የዘብዴዎስ ልጅ ያዕቆብ በዕረፍተ ሰላም ይኽን ዓለም ቢሰናበቱ፤  ታላቁ ነቢይ ኤልያስና ተወዳጁ ደቀ መዝሙር ዮሐንስ ወደ ብሔረ ሕያዋን ተጠርተዋልና…  በኋላው መንገዳቸው ያላቸውን ተዛምዶ ሊያሳይ አወዳጅቶ አገናኛቸው ተገናኛቸውም ይላሉ።

መ) ከዜማ ቤቱ ደግሞ ዮሐንስን በብሔረ ሕያዋን አየሁት የሚለን ቅዱስ ያሬድ ነው። በድጓው ደጋግሞ ምስክርነቱን ሠጥቶናል
«ይኔጽር ዓየራተ
ይነግር ኅቡዓተ
እንዘ ይጽሐፍ በእደዊሑ ዘወንጌል ቃላተ
በቅናተ እግዚኡ ሐቌሁ ቀነተ
ዮሐንስ ድንግል ዘኢጥዕመ ሞተ »
【ከምድር በላይ ጠፈሩን ይመለከታል ፣ የተሰወረውን ይናገራል በእጆቹ የወንጌልን ቃል እየጻፈ በጌታው መታጠቂያ ወገቡን ታጠቀ ፤ በንጽሕና የኖረው ድንግል ዮሐንስ ሞትን ያልቀመሰ ነው! 】
【በድጓ በግእዝ አርያሙ ክፍል ለጥር ፬ቱ ቁመት መነሻ እንዲሆን የጻፈልን ነው። ብራና ገጽ ፻፺፩】

ቅዱስ ያሬድ  በሌላም ሥፍራ ከሞት ተለይቶ እንደመላእክቱ በሕይወት አለ ሲል ዳግመኛ ምስክርነቱን እንዲህ እያለ  ያጸናዋል  «በንጽሕ ከመ መላእክት ተሠርገወ ወእመዊት ከማሆሙ ሐይወ » 【እንደ መላእክቱ ንጽሕናን የተሸለመ ነው ከሞቶም ተለይቶ እንደነሱ በሕይወት አለ】

ሠ) በመልኩ ክፍልና በገድለ ሐዋርያት ማጠቃለያ እንዲሁም በስንክሳራችን የመሰወሩ ምስክርነት ተቀምጦ እናገኛለን 

መልክአ ፍቁረ እግዚእ በመጨረሻዎቹ ሁለት ክፍሎች እንዲህ የሚል ድርሰት እናገኛለን ፦

« ሰላም ለፍልሰትከ ዮሐንስ ሕያው፤
በከመ ወፅአ ነገር እምኀበ አኃው፤
በቅድስና ወበንጽሕ አባላቲከ ሥርግው፤
አብሀኒ ለነሶሳው በውሳጤ ገነት ፍትው፤
ኀበ ይነብሩ ስንዓ ኅሩያን ዕደው።»

【 በወንድሞች ዘንድ አይሞትም የሚለው ይህ ነገር ወጣ እንደተባለ ያልሞትህ ቅዱስ ዮሐንስ ሆይ! ለፍልሰትህ ሰላምታ ይገባል፤ በቅድስና እና በንጽሕና ሰውነቶችህ የተጌጡ ናቸው፤ በሚወደድ በገነት ውስጥ ለመመላለስ አሰልጥነኝ/አብቃኝ፤ በዚያ የሚኖሩ የተመረጡ ወገኖች ናቸውና።】

«ሰላም ለልብስከ ወለአሣእኒከ ደርገ፤
ተዝካረ ሕይወትከ ያዑቅ ለአብሮኮሮስ ዘተኃድገ፤
ዮሐንስ ዘኮንከ ምስለ መላእክት ዘውገ፤
ምሉዓ ወድግዱገ ዘሰላምከ ፈለገ፤
በውሣጤ ከርሥየ ኢይኩን ንቱገ፡፡ »

【የመኖርህን ነገር ያስረዳ ዘንድ ለተተወ ፤ ለልብስህ ከጫማህ ጋር ክብር  ይገባል፤ ከመላእክት ጋር ወዳጅ የሆንክ ዮሐንስ ሆይ! ሞልቶ የተትረፈረፈ የፍቅር አንድነትህ ወንዝ በሆዴ ውስጥ  የጎደለ አይሁን /ይሙላ/።】

ከላይ በተመለከትናቸው የመልክእ ምስጋና ክፍሎች ውሥጥ ቀደምት አበው ሞትን ሳይቀምስ መፍለሱን ወደብሔረ ህያዋን መድረሱን አስረግጠው አኑረዋል፤ በገድሉም በስንክሳሩም የተነገረው ከዚሁ ጋር አንድ ነው

«ወሶበ አእመረ ብፁዕ ዮሐንስ ከመ ቀርበ ፍልሰቱ እምዝንቱ ዓለም ፀውዖሙ ለሕዝብ ወሠርዐ ቍርባነ ወመጠዎሙ ምሥጢራተ ቅድሳት ወአዘዞሙ ከመ ይፅንዑ ውስተ ሃይማኖት ርትዕት ወናዘዞሙ ወባረኮሙ። ወእምዝ አዘዞ ለረድኡ አብሮኮሮስ ወለ፪ቱ ላእካን እምአኀው ከመ ይንሥኡ መካርየ ምስሌሆሙ ወይትል ውዎ ወወፅአ ኀበ አፍአ ሀገረ ኤፌሶን ንስቲተ ወአዘዞሙ ከመ ይክርዩ ግበ ወወረደ ውስተ ግብ ወአውፅአ አልባሲሁ እምላዕሌሁ ወኢተርፈ ላዕሌሁ ዘእንበለ ፩ ቀሚስ ዘሰንዱን። ወአንሥአ እደዊሁ ውስተ ሰማይ ወጸለየ ወአስተፋነዎሙ ከመ ይትመየጡ ውስተ ሀገር ወይንግርዎሙ ለአኀው ከመ ይፅንዑ ውስተ ሃይማኖት ዘክርስቶስ። ወይግበሩ ምግባራተ ሠናያተ እስመ ሀለዎ እግዚአብሔር ይፈድዮሙ ለኵሎሙ ለለ፩ በከመ ምግባሮሙ።  ወይቤሎሙ ካዕበ ንጹሕ አነ እምደምክሙ እስመ ኢያንተጉ ምንተኒ እምት እዛዛቲሁ  ለእግዚአብሔር  ልዑል ወእም ኵሉ ሥርዓቱ ዘይደልወክሙ ወአንትሙ እምይእዜ ኢትሬእዩኒ ገጽየ ግሙራ።  ወሶበ ይቤ ዘንተ በከዩ ወተአምኁ እደዊሁ ወእገሪሁ ወኀደግዎ ውስተ ግብ ወሖሩ ውስተ ሀገር ወነገርዎሙ ለኵሎሙ አኀው። ወሶበ ሰምዑ ነደ ልቦሙ በኀዘን ወሮፁ ወኀሠሥዎ ወኢረከቡ መቃብረ አላ ረከቡ አሣእኖ ወ፩ ልብሶ። ወሰብሕዎ ለእግዚአብሔር  ወአንከሩ ምግባራቲሁ ዘአ ዕረፎ ለረድኡ ዮሐንስ በዝንቱ ዕረፍት ሠናይ።»

         【የተመሰገነ ዮሐንስም ከዚህ ዓለም የሚወጣበት ሰዓት እንደ ቀረበ በአወቀ ጊዜ ሕዝቡን ጠራቸው ጸሎትንም ጸለየና ኅብስቱን ባርኮ ቆረሰ ይህም የጌታችን ሥጋውንና ደሙን ሰጣቸው በቀናች ሃይማኖትም እንዲጸኑ አዘዛቸው ባረካቸው አጽናናቸውም ።  ከዚህም በኋላ ደቀ መዝሙሩ አብሮኮሮስን ከወንድሞችም ሌሎች ሁለትን መቆፈሪያ ይዘው ይከተሉት ዘንድ አዘዘ ። ከኤፌሶንም ከተማ ውጭ ወጣ ጕድጓድ እንዲቆፍሩም አዘዘ ከውስጥዋም ወርዶ ቆመ ልብሱንም አስወገደ ከአንድ የበፍታ ቀሚስ በቀር አላስቀረም ። እጆቹንም አንሥቶ ጸለየና ወደ ከተማ ይመለሱ ዘንድ አሰናበታቸው በክርስቶስም ሃይማኖት ይጸኑ ዘንድ ለሕዝቡ ይነግሩአቸው ዘንድ አዘዛቸው በጎ ሥራዎችንም ይሠሩ ዘንድ ጌታችን ለሁሉም እንደ ሥራው ይከፈለው ዘንድ አለውና ። ሁለተኛም እንዲህ አላቸው እኔ ከሁላችሁም ደም ንጹሕ ነኝ ከእግዚአብሔር ትእዛዝና ሕግ ሳልነግራችሁ የተውኩት ምንም ምን የለምና እናንተም ከእንግዲህ ከቶ ፊቴን አታዩኝም ። ይህንንም በተናገረ ጊዜ አለቀሱ እጆቹንና እግሮቹን ስመው በጒድጓዱ ውስጥ ትተውት ወደ መንገድ ተመለሱና የሆነውን ሁሉ ለሰዎች ነገሩዋቸው ሁሉም ደንግጠው መጡ ግን ልብስና ጫማ እንጂ መቃብሩን አላገኙም እጅግም አደነቁ ደቀ መዝሙሩ ዮሐንስን በዚህ በጎ ዕረፍት ያሳረፈው እግዚአብሔርንም አመሰገኑት ። 】

ረ) የሊቃውንት ቅኔ ለጊዜው በዝክረ ሊቃውንት ከተዘገቡት ሁለቱን ልጠቁም (ጉባኤ ቃናና ዘአምላኪየ)

«ዘማ መቅበርት ለወልደ ነጎድጓድ ትቤሎ፤
እመ ትጸልአኒ አንተ ዘያፈቅረኒ ሀሎ»
(ዘማ የሆነች መቃብር ዮሐንስን እንዲህ አለችው አንተ ብትጠላኝም የሚያፈቅረኝ አለኮ)

tg-me.com/orthodox1/13011
Create:
Last Update:

BY ኦርቶዶክስ ተዋህዶ - ‌🇴‌🇷‌🇹‌🇭‌🇴‌🇩‌🇴‌🇽 ‌🇹‌🇪‌🇼‌🇦‌🇭‌🇩‌🇴

Warning: Undefined variable $i in /var/www/tg-me/post.php on line 283

Share with your friend now:
tg-me.com/orthodox1/13011

View MORE
Open in Telegram

ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ‌🇴‌🇷‌🇹‌🇭‌🇴‌🇩‌🇴‌🇽 ‌🇹‌🇪‌🇼‌🇦‌🇭‌🇩‌🇴 Telegram | DID YOU KNOW?

Date: |

How Does Bitcoin Mining Work?

Bitcoin mining is the process of adding new transactions to the Bitcoin blockchain. It’s a tough job. People who choose to mine Bitcoin use a process called proof of work, deploying computers in a race to solve mathematical puzzles that verify transactions.To entice miners to keep racing to solve the puzzles and support the overall system, the Bitcoin code rewards miners with new Bitcoins. “This is how new coins are created” and new transactions are added to the blockchain, says Okoro.

Telegram Be The Next Best SPAC

I have no inside knowledge of a potential stock listing of the popular anti-Whatsapp messaging app, Telegram. But I know this much, judging by most people I talk to, especially crypto investors, if Telegram ever went public, people would gobble it up. I know I would. I’m waiting for it. So is Sergei Sergienko, who claims he owns $800,000 of Telegram’s pre-initial coin offering (ICO) tokens. “If Telegram does a SPAC IPO, there would be demand for this issue. It would probably outstrip the interest we saw during the ICO. Why? Because as of right now Telegram looks like a liberal application that can accept anyone - right after WhatsApp and others have turn on the censorship,” he says.

ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ‌🇴‌🇷‌🇹‌🇭‌🇴‌🇩‌🇴‌🇽 ‌🇹‌🇪‌🇼‌🇦‌🇭‌🇩‌🇴 from ru

Telegram ኦርቶዶክስ ተዋህዶ - ‌🇴‌🇷‌🇹‌🇭‌🇴‌🇩‌🇴‌🇽 ‌🇹‌🇪‌🇼‌🇦‌🇭‌🇩‌🇴
FROM USA